በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ […]
ምድብ፥ News
የኤማሁስ መንገደኞች
የሁለት ሰዎች ወግ እንመልከት 1. ለመሆኑ እነዚህ ሁለት መንገደኞች እነማን ናቸው? 2. የሚነጋገሩት ርዕሰ ጉዳይስ ምን ነበር? 3. በመካከላቸው ተገኝቶ […]
ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት)
በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖና መሰረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በግሪክ ቋንቋ ኒቆዲሞስ ማለት “አሸናፊ/ነት” ማለት ነው፡፡ በዚህ ሰንበት በዮሐ 3፡1-21 እንደተገለጸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ አለቃ ያስተማረው ትምህርት እንዲሁም የኒቆዲሞስ አስተማሪ ስብእና ይነበባል፣ ይተረጎማል፣ ይዜማል፡፡
ገብርኄር (የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት)
ታላቁን የጌታችንን ጾም ከጀመርን ስድስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር ጠቃሚ ነው፡፡
ደብረ ዘይት (የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዓለ ደብረ ዘይት የደብረ ዘይት ትርጉም ከትርጉሙ ለመነሣት ደበረ ዘይት ማለት ትርጉሙ […]
መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የማዳኑ ጉዳይ ጎልቶ ከሚነገርባቸው ጊዜያት አንዱ ይህ “መጻጉ’’ የተሰኘው […]
ምኩራብ ( የዐቢይ ጾም ሶስተኛ ሳምንት )
በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖና መሰረት የዐቢይ ፆም ሦስተኛ ሳምንት “ምኩራብ” ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም […]
ቅድስት ( የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት )
“ቅድሰት” የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ቅድስት ማለት የዘይቤ ፍችው የተቀደሰች፤ የተለየች ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት የሆነችው ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል (ማቴ. 4-2) ። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡
ዘወረደ (የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት)
ዘወረደ(ጾመ ሕርቃን) «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ […]