የብፁዕነታቸው መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

«ዘይፌኑ ቃሎ ለምድር፣ ወፍጡነ ይረውፅ ነቢቡ = ቃሉን ወደ ምድር ይልካል፥ ነገሩም እጅግ ፈጥኖ ይደርሳል» (መዝ. 147፥15)።

እንግዶቻችን በፈለጋችሁበት ሠዓትና ጊዜ ሁሉ በያላችሁበት ሁናችሁ ማዕደ እግዚአብሔርን ወደምትመገቡበትና ስለ ደብራችን መረጃ ወደምታገኙበት ፈጣን መስተናገጃ ድረ-ገጻችን እንኳን ደኅና መጣችሁ!

ከላይ የተጠቀሰው የነቢዩ ዳዊት ትንቢት እየተፈጸመ የሚገኘበት ዘመን ቢኖር ይህ የመረጃና የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። በአንድ ዐውደ ምሕረት የቀረበው የእግዚአብሔር ቃል እና የሚፈለገው መንፈሳዊ መረጃ በመላው ዓለም ፍጥኖ የሚደርስበት እና ወደፈለጉት ሰዎች ጆሮ ሁሉ በተመሳሳይ ሰዓት የሚደርስበት አስደናቂ ዘመን! ስለሆነም የቃሉ መንፈሳዊ ማዕድና የሚፈለገው መረጃ ያለ ወረፋ ለሁላችሁም በእኩልነትና በተመሳሳይ ሰዓት በፊታችሁ የሚቀርብበት መንፈሳዊ ዐውደ ማዕድ እነሆ።  የሁሉ ፈጣሪና መጋቢ ኃያል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር ያመጣው እና በበጎነት እንዲገኝና እንዲኖር የሚባርከው በቃሉ ነው። ለፍጥረቱ በቃሉ ሕይወትን ይሰጠዋል፣ በቃሉ ይመራዋል፣ በቃሉ ያፀናዋል፣ በቃሉ ያከብረዋል፣ በቃሉ ይቀድሰዋል፣ በቃሉ ይመራዋል፤ በጠቃላላው የምድር ቀዳሚ በረከቷ የፈጣሪዋ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

በዚህ መልእክት ዐውድ መሠረት  ምድር ስንል በዋናነት  ለሰማያዊነት የተመረጠው ለጊዜው በሥጋ ወደምድር ልብ የሚመለሰውንና በነፍሱ ደግሞ ወደሰጠው ወደ እግዚአብሔር የሚመለሰውን በኋላም በነፍሱም በሥጋውም በተዋሕዶ በክብር ተነሥቶ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ የሚያደርገውን ሰውን ማለታችን ነው። የተገኘም ከምድር ወይም ከመሬት ሲሆን እስከ ትንሣኤ ዘጉባዔ ድረስ በሥጋው የሚመለሰውም ወደመሬት ነውና።

ለፈጥረቱ የሚራራና የሚያዝን እግዚአግብሔር የፍጥረት ሕይወት ኃይልና ብርታት የሆነውን የቃሉን በረከት የሚያዳርስበትን ዐውደ ምሕረት እያሰፋው ይገኛል። ከቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ዐውደ ምሕረት በዘመናችን ሰጥቶናል። በኖርዌይ ኦስሎ የሚገኘው መካነ ቅዱሳን ቅ/ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ በድረ ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን

አባ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ

«የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን» (ነህ. 2፥20)

አሠራራችን

በእያመቱ ዓመታዊ ዕቅድና በጀታችንን አዘጋጅተን ለጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባዔው በመጨረሻም ለሀገረ–ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ኤልያስ እያቀረብንና እያጸደቅን እንሠራለን። በዓመት ፪ ጊዜ ማለትም በየ ፮ ወሩ ለጠቅላላ ጉባዔው እንዲሁም ለሀገረ–ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ኤልያስ የሥራ ክንውንና የሂሳብ ሪፖርት እናቀርባለን። ከላይ የተጠቀሱት የአገልግሎት ክፍሎች ዓመታዊ ዕቅዳቸውን እና የሥራ ክንወን ሪፖርታቸውን በወቅቱ ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔው እንዲያቀርቡ እየተደረገ ተጠቃሎ እና ተጭምቆ ለበላይ አጽዳቂ ክፍሎች እዲቀርብ እየተደረገ የአፈጻጸም እንቅሥቃሴው ይካሄዳል።

ርእያችን

ከተለመደው «ራእይ» ከሚለው ይልቅ «ርእይ» የሚለው ቢለመድ ከትርጉሙና ለማለት ከፈለግነው አንፃር ተስማሚ ይሆናል። ርእይ ትርጉሙ፦ ማሰብ፣ መመኘት፣ መገምገም፣ መገመት፣ … ማሟረት፣ ትንቢት መናገርና መላ መምታት ማለት ነው። በዓይነ ልብ የሚታይ ሕልማዊ መልክ አለው። «ራእይ» ደግሞ መልክ፣ ፊት፣ ቅርፅ እና ገጽ ዓይነ ሥጋ የሚያርፍበት ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መ/ሰ/ወ/ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ (ገጽ ፰፻፲፮)

ርእያችን በአንድ ዐረፍተ–ነገር ሲገለጽ፦ በማንኛውም መንገድ በብቃቱና በጥራቱ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ቤተ–ክርስቲያን መገንባት ነው።

0

ክፍሎች

0

ንዑስ ክፍሎች

0

አገልጋዮች

የሰ/መ/አ/ጉ አባላት

ቤተ ክርስቲያናችንን ከ 2022 ጀምሮ በሰበካ አባልነት እያገለግሉ ያሉ