የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በኖርዌይ
መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
ስለ ቤተ ክርስቲያናችን
አመሰራረትና እድገት
በሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ መልካም ፍቃድ እና የቡራኬ ሥርዓት በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ወይንም እ.ኤ.አ. በ1995 G.C. ተመሠረተች። በ 2017 G.C. የራሷ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገዛች።
ልዩ ልዩ ክፍሎች
የቤተ ክርስቲያናችን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በ 6 ክፍሎችና በ 16 ንዑስ ክፍሎች እራሱን አደራጅቶ እየሠራ ይገኛል። እንዲሁም ሰንበት ት/ቤታችን 6 ክፍሎችና 12 ንዑስ ክፍሎት አሉት።
መተዳደርያ ደንብ
ቤተ ክርስቲያናችን ከተመሠረትችበት ጀምሮ ርእይዋን፣ የምእመናን ፍላጎትና ጊዜን በዋጀ እንዲሁም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያንን ቃለ አዋዲ በተከተለ መልኩ እየተሻሻለ የመጣ መተዳደርያ ደንብ አላት።
የአባልነት ፎርም
ቤተ ክርስቲያናችን የአባልነቱ ቅጽ በትክክል ተሞልቶ ሲደርሳት አባልነትን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ተሰጣለች። ይህም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኖርዌይ አባል መሆንዎን ያረጋግጣል።
የሚሰጡ አገልግሎቶች
ቤተ ክርስቲያናችን የቅዳሴ፣ የጸሎት፣ የምህላ፣ የክርስትና፣ የፍትሃት፣ የጋብቻ እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ትሰጣለች። በተጨማሪም የአብነት ት/ርት የአማርኛ ቋንቋ ት/ርት እየሰጠች ትገኛለች።
ቤተ ክርስቲያንችንን ለመደጎም
የቤተ ክርስቲያናችን ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከምእመናን የምታገኛቸው ወርሃዊ መዋጮዎች፣ አስራት በኩራት እና ሙዳዬ ምጽዋት ናቸው። በተጨማሪም በአባላት ቁጥር ልክ ከኖርዌይ መንግሥት ድጎማ ታገኛለች።
የሰ/መ/አ/ጉ
ከጠቅላላ ጉባኤው ቀጥሎ የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አመራር ነው
በቃለ አዋዲው አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 17 መሠረት አንድ ጽ/ቤትና ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች አቋቁሞ እየሠራ ይገኛል
በቃለ አዋዲው አንቀጽ 5 እና 6 የተደነገጉትን ተግባራት እያከናወነ ይገኛል
በወር ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል
የቤተ ክርስቲያኒቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎችን እየሠራ፣ እያስተባበረ እና አመራር እየሰጠ ይገኛል
የተመዘገቡ አባላት
ወርሃዊ ክፍያ የሚከፍሉ
“ሕፃናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው” ሉቃ ፩፰፥፮
ሰንበት ት/ቤት
ዘወትር እሑድ ከቅዳሴ በኋላ መንፈሳዊ ት/ርት በቤተ ክርስቲያናችን ይሰጣል።
የአብነት ት/ርት
ማክሰኞ (16:00) እና ዓርብ (17:00) በቤ/ክ እንዲሁም ቅዳሜ (10:00) በዙም ይሰጣል።
የመዝሙር ጥናት
ዘወትር ረቡዕ (20:30) እና ሐሙስ (19:30) በዙም ይሰጣል።
የቤተ ክርስቲያናችን ሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ልጆቻችን ሃይማኖታቸውን፣ ቋንቋቸውንና ባህላቸውን አውቀውና ጠብቀው እንዲያድጉ እየተጋ ይገኛል
ወቅታዊ ኹነቶች
በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን የሚደረጉ ዋና ዋና ክስተቶች፣ ዜናዎች እንዲሁም ማስታወቂያዎች ከዚህ ይገኛሉ።