ጋምለ ኦስሎ አካባቢ በ16 ሚሊዮን ክሮነር ለሽያጭ የወጣ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተገኝቷል! ለተጨማሪ መረጃ ቀጥሎ ያሉትን ሊንኮች ይመልከቱ::
https://www.finn.no/realestate/homes/ad.html?finnkode=106071303
ይህን በተመለከተ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2010 ዓ/ም ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴና ሰበካ ጉባኤ እጅግ አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ አድርገው ሰፊ ውይይት አድርገዋል:: በመጨረሻም በተጠቀሰው ዋጋ በከተማዋ አማካኝ ቦታ ላይ እንዲህ አይነት ሕንፃ ማግኘት እጅግ ጥሩ ዜና መሆኑን ግንዛቤ ተወስዷል::
ሕንፃውን ለመግዛትም መጫረት እንዳለብን በሙሉ ድምጽ ተወስኗል:: ጫረታውን ለማሸነፍ ከባንክ ብድር ማግኘት ወሳኝ ነው! ባንክ የምንፈልገውን ያህል እንዲያበድረን ምእመናንና ምእመናት ለቤተ ክርስቲያናቸው በቋሚነት የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ይመለከታል:: በመሆኑም እርስዎ እስካሁን አሥራት ለመክፈል ቅጹን ካልሞሉ አሁኑኑ ይህን ሊንክ http://www.eotcnor.no/asrat/ክሊክ በማድረግ ቅጹን ይሙሉና ይላኩልን! ነገ ሰኞ ጠዋት ባንክ ከመሄዳችን በፊት ዛሬውኑ ቅጹን ሞልተው ይላኩልን! ተጨማሪ ማብራሪያ በመጪው እሑድ እናቀርባለን::
የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት