የገና ስጦታ ለቤተ ክርስቲያናችን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ቤተ ክርስቲያናችን ኮሮና ወረርሽኝ ከተነሣ ጀምሮ መንፈሳዊ አገልግሎትን ሳታቋርጥ ለምእመኑ እየሰጠች እንዲሁም በስብከት እያስተማረች ፣ እየመከረች እና እያጽናናች ትገኛለች። ከዚህ ከመከራና ከበሽታ ጊዜ ጠብቆ ለዚህ ቀን ስላደረሰን ስሙ የከበረ የተመሰገነ ይሁን! እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያናችን ህንፃ በቅርብ ጊዜ የተገዛና በከፊል እዳ ያለበት ስለሆነ ፣ የቤ/ክን የገቢ ምንጭም አባላት ስለሆንን ፤ ሁላችንም ለአገልግሎቱ መፋጠንና መኖር እናግዝ ዘንድ እጃችንን ለቤተክርስቲያን እንዘርጋ። በየዓመቱ ለልጆቻችን የገና ስጦታ እንደምንሰጥ ይታወቃል ፣ እኛም ለቤተ ክርስቲያናችን የገና ስጦታ እናበርክት ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለዚህ ይረዳን ዘንድ በቪፕስ ቁጥር Vipps 616461 Julegave ብለን እንላክ ። ወይንም በባንክ ቁጥር 12031901535 የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ከታህሣሥ 20/2020 እስከ ጥር 7/2020 ይቆያል።