ጫረታ ስለመራዘሙ

ብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

«የሚያገለግልም ቢሆን እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል» (1ጴጥ 4:11)

ለሽያጭ የወጣው ሕንፃ እጩ ገዥዎች የመጨረሻ የሚጎበኙበት ቀን ኦክቶበር 31ጫረታ የሚጀመረው ደግሞ ኖቬምበር 1 ቀን እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል:: ይሁንና ኦክቶበር 31 ቀን ከሰዓት በኋላ ከደላላው አዲስ መልእክት ደርሶናል:: በመሆኑም የመጨረሻ ጉብኝት ኖቬምበር 1 ቀን 16 እስከ 17 ሰዓት ተኩል ይደረግና ጫረታው ኖቬምበር 6 ቀን በመጪው ሰኞ እንደሚካሄድ ታውቋል::

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የጀመርነውን ዝግጅት አጠናክረን እንደምንቀጥል ስንገልጽላችሁ የእናንተን ሁሉ ታሪካዊ ትብብር በመተማመን ነው!

እስካሁን ላደራጋችሁት አኩሪ ሥራ እግዚአብሔር ይስጥልን! ምስጋናችንም እጅግ የላቀ ነው!

«የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል። እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን» (ነህ 2:20)

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በኖርዌይ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ