በመላው ዓለም ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ጥሪ!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

https://www.gofundme.com/eotcnor

ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው።

በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በ1900 ዓም የተገነባ እና ጥንታዊ ይዘቱን ሳይለቅ በ1990ዎቹ በሚገባ የታደሰ በ730 ካሬ ላይ የሰፈረ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ከፍተኛ ርብርብ ላይ ነች።ጨረታው በ72 ሰዓታት ውስጥ ይደረጋል።ለጨረታው የሕንፃ ኮሚቴ ካለው ገንዘብ እና የባንክ ብድር በተጨማሪ የተወሰነ ገንዘብ ያስፈልገዋል።ቅርሱ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ባለፈ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አንደምታ አለው። ስለሆነም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን ለጥቂት ሰዓታት የተከፈተ ጎ ፈንድ አካውንት የአቅማችሁን በመስጠት ከበረከቱ ተካፈሉ። ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው።

በኖርዌይ ኦስሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ከበረከቱ ለመሳተፍም ሆነ የታሪኩ አካል ለመሆን ከስር የተለጠፈውን ተጭነው በ”ጎፈንድ” አካውንት አስተዋፅኦ ያድርጉ።

https://www.gofundme.com/eotcnor