የበኩላችሁን ልዩና ታሪካዊ ርብርብ ማድረግ ትችሉ ዘንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በኖርዌይ ለቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ!
ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ሊሆን የሚችል ሕንፃ በድንገት ለሽያጭ መቅረቡን ማሳወቃችን ይታወቃል! ይህን በተመለከተ ቀደም ብለን ባስተላለፍነው ማስታወቂያ መሠረት ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ/ም ማዮሽቱዋ ቤተ ክርስቲያን ሰፊ ውይይት ተደርጓል:: የመፍትሔ ሃሳቦችም ተለይተው ወደ ሥራ ተገብቷል:: ጫረታውን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ማሸነፍ የምንችለው ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በሚችሉት ሁሉ ሲሳተፉ ነው:: በመሆኑም የበኩላችሁን ልዩና ታሪካዊ ርብርብ ማድረግ ትችሉ ዘንድ አማራጭ መፍትሔዎች ተለይተዋልና በስልክ ቁጥር 99479730 በመደወል መረጃ ጠይቁ:: በመረጃውም መሠረት ወዲያውኑ ወደሥራ ግቡ! በተጨማሪም በመጪው እሑድ ከቅዳሴ ቀጥሎ በዚሁ ጉዳይ ላይ ምክክር ስለምናደርግ በሰዓቱ እንድትገኙ ቤተ ክርስቲያናችሁ ጥሪዋን ታስተላልፋለች

ብፁዕ አባ ሕርያቆስ