እጅግ አስቸኳይ ጉዳይ ለኦስሎ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ!

ጋምለ ኦስሎ አካባቢ በ16 ሚሊዮን ክሮነር ለሽያጭ የወጣ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተገኝቷል! ለተጨማሪ መረጃ ቀጥሎ ያሉትን ሊንኮች ይመልከቱ::

https://www.vartoslo.no/kunne-du-tenke-deg-et-menighetshus-i-oslos-gamleby-ta-med-16-millioner-lop-og-kjop/

https://www.finn.no/realestate/homes/ad.html?finnkode=106071303

ይህን በተመለከተ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2010 /ም ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴና ሰበካ ጉባኤ እጅግ አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ አድርገው ሰፊ ውይይት አድርገዋል:: በመጨረሻም በተጠቀሰው ዋጋ በከተማዋ አማካኝ ቦታ ላይ እንዲህ አይነት ሕንፃ ማግኘት እጅግ ጥሩ ዜና መሆኑን ግንዛቤ ተወስዷል::

ሕንፃውን ለመግዛትም መጫረት እንዳለብን በሙሉ ድምጽ ተወስኗል:: ጫረታውን ለማሸነፍ ከባንክ ብድር ማግኘት ወሳኝ ነው! ባንክ የምንፈልገውን ያህል እንዲያበድረን ምእመናንና ምእመናት ለቤተ ክርስቲያናቸው በቋሚነት የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ይመለከታል:: በመሆኑም እርስዎ እስካሁን አሥራት ለመክፈል ቅጹን ካልሞሉ አሁኑኑ ይህን ሊንክ http://www.eotcnor.no/asrat/ክሊክ በማድረግ ቅጹን ይሙሉና ይላኩልን! ነገ ሰኞ ጠዋት ባንክ ከመሄዳችን በፊት ዛሬውኑ ቅጹን ሞልተው ይላኩልን! ተጨማሪ ማብራሪያ በመጪው እሑድ እናቀርባለን::

የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት