፲፱ኛው የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባዔ

Dato: March/03/2016
የካቲት ፳፭/፳፻፰ ዓ/ም የፋ.ቁ 009/2016

ለምእመናን በሙሉ።
ጉባዔውን አውጁ (ኢዩ. ፪፥፲፬)።

ጉዳዩ፦ ፲፱ኛውን የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባዔ ይመለከታል።
በቅድሚያ የእግዚአብሔር ሰላምና ጸጋ እንዲበዛላችሁ የዘወትር ጸሎታችንና ምኖታችን ነው። ፲፱ኛው የአውሮፓ ታላቁ መንፈሳዊ ጉባዔ በ2016 በኦስሎ ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦ/ ተዋሕዶ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን እንደሚካሄድ ይታወቃል።
በመሆኑም ጉባዔውን ለሚካፈሉ ሁሉ የሚካሔድበትን ጊዜ ከወዲሁ ማብሠር አስፈላጊ ስለሆነ እንደ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ከሰኔ 24-26, 2016 (17-19፣2008 ዓ/ም) የሚካሄድ መሆኑን እየገለጽን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በተጨማሪም ተጋባዥ መምህራንን፣ ዘማሪያንና ቀሪ ኢንፎርሜሺኖችን በተመለከተ በሚቀጥለው ጊዜ የዚሁ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ የግንኙነት ክፍል በተከታታይ በሚያወጣው ማስታወቂያ የሚገለጽ መሆኑንም በትሕትና እናሳውቃለን።

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን
በኦስሎ ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ሰ/መ/አ/ጉባዔ ጽ/ቤት።
ኦስሎ ኖርዌይ