ለእመናን በሙሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቅዱስ ገብርኤል እና የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ለዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያለች በዓብይ ጾም ወቅትም ዘወትር ረቡዕ እና ዓርብ ከ17:00 እስከ 19:00 ሰዓት ድረስ ጸሎተ ምሕላ ታደርሳለች። ስለዚህም ምእመናን በሙሉ በቤተ ክርስቲያኗ በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊዎች ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን ከወዲሁ እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የቤተ ክርስቲያን ሰ.መ.ጉባዔ