እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ

እንን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቅ/ገብርኤል እና የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጥምቀትን በዓል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር ፲፫ እና ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም (January 21-22, 2017) ቅዳሜና እሑድ በደመቀ ሁኔታ ያከብራል፡፡ በመሆኑም:-

1ኛ/ ቅዳሜ ጥር ፲፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም (January 21/2017) ከቀኑ 17 ሰዓት ላይ ታቦታት ወጥተው ከተራ ይሆናል። ከሌሊቱ ፱ ሰዓት (3 am) ጀምሮ ማኅሌት ይኖራል።

2ኛ/ እሑድ ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ቅዳሴ እና የጥምቀተ ባሕር ሥነ-ሥርዓት ከማለዳው ፲፪ ሰዓት (6 am) ጀምሮ ይኖራል።

በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የአውሮፓ፣ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ እንዲሁም የአካባቢው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ።

በመሆኑም ምእመናን በሙሉ በተጠቀሱት ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ የበዓሉ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን ከወዲሁ እናስተላልፋለን።

ቦታ: ኦስሎ ማዩሽቱዋ

አድራሻ: Kirkeveien 84,0364,Oslo.