የተገዛው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት ቅድመ-ዝግጅት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በኖርዌይ የቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ የ2018 /ም ዓላማ የተገዛውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የአባላትን ብዛትና የአገልግሎት ስፋት እንዲሁም የኖርዌይን የአየር ጠባይ በሚመጥን መልኩ ማዘጋጀት እና ተያያዥ ወጪዎችን መሸፈን ነው። በተጨማሪም የተገዛው ሕንፃ ገቢ የሚያስገኝበትን ሁኔታ አጥንቶ ለውይይትና ለውሳኔ ያቀርባል አፈጻጸሙንም ይከታተላል።

ሕንፃውን ለግንቦት 12 የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ንግስ ዝግጁ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው። በተለይም የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ የምህንድስና ክፍል ልዩ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል! ተጨማሪ ከእድሳት ጋር የተያያዙ ወዎችን ለመቀነስ በተፈለገው ጊዜ ሥራዎችን ለማከናወን ይቻል ዘንድ ኮሚቴው ቀለም ቀቢዎችን፣ የቧንቧ ሠራተኞችን፣አናፂዎችን፣ግንበኞችን፣ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎችን፣ ቬንትሌሽን፣ ፍሊሰና ሌሎችንም የቴክኒክና የምህንድስና ባለሙያዎችን አብዝቶ ይፈልጋልና ሙያው ያላችሁ ልዑል ዓለማዬሁን ወይም /ር ይስሃቅን አናግራችሁ እንድትመዘገቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ከዚያም ሥራው ከመጀመሩ በፊት ቀድመን የሚመቻችሁን ጊዜ እየጠየቅን እንመድባችኋለን!

ለበለጠ መረጃ የምህንድስና ክፍል ሓላፊን ኢ/ር ይስሀቅን በስልክ ቁጥር 97592932 ማነጋገር ትችላላችሁ።

እንዲሁም መጋረጃ ምንጣፍና ሌላም ስጦታ በአይነት ማቅረብ ያሰባችሁ እንዳላችሁ ከዚህ በፊት አሳውቃችሁናል ለዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው! ወጥነት ባለው እንዲሁም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ባማከለ መልኩ ሁሉ ነገር ይከናወን ዘንድ ስለሚያስፈልግ በማናቸውም መልኩ ለተገዛው ሕንፃ እድሳት አስተዋጽዖ ማድረግ የምትፈልጉ ሁሉ ካሁኑ እንድታቅዱና እንድትመዘገቡ ስናሳስባችሁ እንደምትተባበሩን በመተማመን ነው። እንዲሁም የገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ የምትፈልጉ የኮሚቴውን ገንዘብ ያዢ ዘቢብ ካሳሁንን በስልክ ቁጥር 96988339 ወይም በአካል ማነጋገር ትችላላችሁ

ያግኙን!

Den Etiopisk Ortodokse Kirke I Norge

Kirkeveien 84

0364 Oslo, Norway

byggkomitte@eotcnor.no

Bankkontonr.: 15034581883

BIC: DNBANOKKXXX

Elektronic IBAN: NO2115034581883

IBAN for use in print: NO21 1503 4581 883

Tel.: 99479730/91139611

ለምታደርጉት ማናቸውም ትብብር ምስጋናችን እጅግ የላቀ ነው!

የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሠራለንነህ 220

የቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ